የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2014 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምማውን የዘርፍ ም/ፕሬዚዳንቶች እና የዩኒቨርሲቲዉ የካዉንስል አባላት በተገኙበት ታህሳስ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በህዳሴ አዳራሽ አካሄደ፡፡
በግምገማዉ መክፈቻ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ ለካውስሉ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ በዚህ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሁሉም የካዉንስል አባለት ክፍተቶችን በመለየት የነጠረ ሀሳብ እንዲያቀርቡ፤ በተለይ በ 6 ወር ዉስጥ የተከናወኑ እና ያልተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር በመለየት ለበለጠ የሥራ አፈጻጸም ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚቀመጡበት የግምገማ መድረክ መሆኑን በማሳሰብ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል ፡፡