$ 0 0 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና ኢንስቲትዪት ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለመጡ የከተማ ልማትና ፕላን ዘርፍ ባለሙያዎች ለአርባ አምስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ ስልጠናውም ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከፌዴራል፣ ከክልል እና የከተማ መስተዳደር የተወጣጡ ባለሙያዎች ይሳተፉበታል፡፡