የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ተመራቂ ተማሪዎች የምረቃ ፅሑፍ አዘገጃጀት ሥነ ዘዴዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና በቀን ህዳር 14-2015 በአባይ አዳራሽ ተሰጠ፡፡
ስልጠናው የተዘጋጀው በስርዓተ-ፆታ እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ሲሆን፤ የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ በ2015 ለሚመረቁ ሴት፣ አካል ጉዳተኛና ከአርብቶ አደር አካባቢ ለመጡ ተማሪዎች በጥናትና ምርምር ፅሑፍ አቀራረብ ዙሪያ መከተል ያለባቸውን መንገዶች ምን መምሰል እንዳለበትና ሊከተሏቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦችን ማስገንዘብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ስልጠናው በተለያዩ መንገዶች በቴሌግራም በኢሜልና በአካል በየአመቱ ለተጠቀሱት ተመራቂ ተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ የሚሰጥ ሲሆን በዚህም ዓመት ለ123 ተማሪዎች ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ በቀጣይም ከዚህ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አቶ ዝናቤ ታደሰ የስርዓተ-ፆታ እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡